Skip to main content
Loading Events

« All Events

  • This event has passed.

የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና የማህበረሰብ ውይይቶች፡ የኮቪድ-19 ክትባቶችን በተመለከተ ቀጥታ ዉይይት

January 12, 2021 @ 3:00 pm - 3:30 pm

ለዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ

በአሁኑ ግዜ ፒፋይዘር እና ሞደርና የተባሉት የኮቪድ -19 ክትባቶች እኛ ጋ የደረሱን ሲሆን አብዛኛዎቹ የስራ ባልደረቦቻችን ክትባቶቹን መውሰድ ጀምረዋል፤ ለሁላችንም ረጅምና አስቸጋሪ የነበረውን ወቅት ለማለፍ እና ወደ ፊት ለመጓዝ በጉጉት እና በተስፋም ላይ እንገኛለን፡፡

የኮቪድ-19 ቫይረስን ለመግታት እነኝህ ክትባቶች አይነተኛ ቀጣይ እርምጃዎች ቢሆኑም ፤ኣብዛኛዎቻችሁ ሰለ ክትባቶቹ መረጃ ከበርካታ ምንጮች ማለትም ከ ዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና፣ ከማህበራዊ ሚድያ ፣ከቴሌቪዥን፣ ከሬዲዮ እና ሌሎች ምንጮች ምናልባትም ከቤተሰብ አባላትና ጓደኞቻችሁ ያገኛችሁ ቢሆንም ብዙዎቻችሁ እነኝህን ክትባቶች በተመለከተ ጥያቄዎችና እና ሃሳቦች እንዳሏችሁ ተገንዝበናል፡፡

ለጥያቄዎቻችሁ እና ሃሳቦቻችሁ መልስ ለመስጠት በርካታ መረጃዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች በ ዙም አማካኝነት በበርካታ የውይይት ክፍለ-ግዜያት እየሰጥን እንገኛለን፡፡ እነዚህ ሁሉም ውይይቶች የሚመሩት በ ዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ዶክተሮች እና የክትባት ኤክስፐርቶች ነው፡፡እነዚህን የውይይት ክፍለ-ግዚያት ያመቻቸን እና እናንተም መሳተፍ እንድትችሉ የመከታተያ ግዜ /ሰዓት/ እንዲፈቀድላችሁ ያደረግን መሆኑን የእናንተ ማናጀሮቻችሁ(አለቆቻችሁ) ያቃሉም፤ ተስማ ምተዋልም፡፡

የዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ህክምና የማህበረሰብ ውይይቶች፡ የኮቪድ-19 ክትባቶችን በተመለከተ ቀጥታ ዉይይት

ማክሰኞ፤ ጃንዋሪ 12 በአማርኛ ፡- ከ3:00 – 3:30pm ከአዝመራ ጥላሁን ጋር

የዙም ውይይት ክፍለ-ግዜ ማስተሳሰሪያ /ሊንክ፡ https://washington.zoom.us/j/93749142152

ለሌሎች ቋንቋዎች የውይይት ክፍለ-ግዜ እባክዎን ከዚህ በታች በተገለፀው ሊንክ/ማስተሳሰሪያ መረጃዎችን ይመልከቱ፡፡

ማንኛውም እና ሁሉም ሰራተኞች፣ተማሪዎች፣ፋከልቲ፣አቅራቢዎች እና ስታፎች እንዲከታተሉ እናበረታታለን፡፡እባካችሁ ጥያቄዎቻችሁን በደንብ አዘጋጅታችሁ ኑ፡፡ውይይቱን የምንጀምረው በአጠቃላ መረጃ ሲሆን ከዛም ወደ ጥያቄዎች እና መልሶች እናመራለን፡፡

መምጣትዎን በጉጉት እንጠብቃለን፡፡

Details

Date:
January 12, 2021
Time:
3:00 pm - 3:30 pm
Event Tags:
,

Organizer